loading
ሶልሻዬር የቲያትር ኦፍ ድሪምስ አለቃነቱ ቋሚ ሆነ

ኖርዌያዊው አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር የማንችስተር ዩናይትድ ቋሚ አሰልጣኝነት በሶስት ዓመታት ውል በክለቡ ፀድቋል፡፡

የ46 ዓመቱ ሶልሻዬር የዦሴ ሞሪንሆን ስንብት ተከትሎ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ታህሳስ ወር ላይ ነበር የዩናይትድ አለቃ መሆን የቻለው፡፡

ከቋሚ የአሰልጣኝነት ሹመት በኋላ ሶልሻዬር ‹‹ ሁሌም ሳልመው የነበረውን ስራ ነው ያገኘሁት፤ ለረዥም ጊዜ ክለቡን ለመምራት ዕድል በማግኘቴም ደስተኛ ነኝ›› ብሏል፡፡

የክለቡ ምክትል ሊቀመንበር   ኢድ ውድዋርድ ሹመቱ ‹‹ ሲበዛ ይመጥናል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኦሌ በኦልድ ትራፎርድ የጥቂት ወራት የጊዜያዊ አሰልጣኝነት ቆይታው፤ ከሊጉ አራት መሪ ክለቦች ደረጃ በ11 ነጥብ ርቆ ስድስተኛ ደረጃ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም፤ በ13 የሊጉ ጨዋታዎች በአርሰናል ሽንፈት ከማስተናገዱ ውጭ ስኬታማ ጉዞ ማድረግ ችሏል፡፡

ክለቡ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በሜዳው በፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ዤርማ ሽንፈት ቢገጥመውም፤ ፓሪስ ላይ ውጤቱን በመቀልበስ ታሪክ በመስራት ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችሏል፡፡

ኦሌ ክለቡን በመራባቸው ሁሉም ጨዋታዎች ዩናይትድ በ14ቱ ድል ሲያደርግ፤ በሶስቱ ብቻ ሽንፈት ገጥሞታል፤ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይቷል፡፡

በአጠቃላይ የቡድኑ የማሸነፍ ጉዞ በአማካይ 73.7 መቶኛ ደርሷል፡፡

ኖርዌያዊው አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ፤ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በ2013 በጡረታ ከማንችስተር ዩናይትድ አለቃነታቸው ከተሰናበቱ በኋላ አራተኛው የቀያቹ ቋሚ አሰልጣኝ በመሆን ተሸሟል፡፡  

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *