loading
ስተርሊንግ የፀረ ዘረኝነት ሽልማትን አግኝቷል

እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ አማካይ ወጣት ተጫዋች ራሂም ሻክሚል ስተርሊንግ ዘረኝነትን በመፀየፍ እና በመቃወም በሚያርጋቸው እንቅስቃሴ በ ቢቲ ስፖርት ኢንዱስትሪ ሽልማትን ትናንት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት እጅ ተቀብሏል፡፡

ስተርሊንግ እርሱ ላይ ሌሎች ጥቁር ተጫዋቾች ላይ በደጋፊዎች፣ በሚዲያዎች እና በሌሎች ላይ የሚሰነዘሩ የዘረኝነት ትንኮሳዎችን በመቃወም እና ድምፁን ከፍ አድርጎ በማሰማት ይታወቃል፡፡  

ራሂም ስተርሊንግ ያገኘው ሽልማት ለወጣት ተጫዋቾች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል፡፡ ‹‹ ለሚመጣው ቀጣዩ ትውልድ ምሳሌ የሚሆን ነገር ማስቀመጥ አለብህ›› ሲል የ24 ዓመቱ ተጫዋች አስታውቋል፡፡  

የአንግሊዝ ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የስተርሊንግ ተግባር በብሪታኒያ ማህበረሰብ ትልቅ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ጠቁሟል፡፡

ስተርሊንግ የ2019 የብሪቲሽ ኢቲኒክ ዳይቨርሲቲ ስፖርትስ ሽልማት በተጨማሪ፤ በተያዘው የፈረንጆች ሚያዚያ ወር መጀመሪያ የብሪታኒያ ስፖርተኞች ኮከብ ተምሳሌት ሽልማት አግኝቷል፡፡

ተጫዋቹ በዘንደሮው የማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ የውስጥ ውድድሮች እና የአውሮፓ መድረክ ላይ ትልቅ ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *