loading
ሳውዲ አረቢያ የጀማል ካሾጊን ጉዳይ ለእኔ ተውልኝ እያለች ነው

ሀገሪቱ ይሄንን ያለችው በሀገሯ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኩል ሲሆን በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ የግድያ ምርመራ ላይ ማንኛውንም አይነት የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማታስተናግድ ሀሙስ ዕለት አስታውቃለች፡፡

የኮሚሽኑ አለቃ ባንዳር ቢን መሀመድ አል- አይባን ፤ በሲውዘርላንዷ መዲና ጄኔቫ በተደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤቶች ስብሰባ፤ ባደረጉት ንግግር ሳውዲ አረቢያ በካሾጊ ጉዳይ ላይ የሚፈተፍቱ ማንኛውም አይነት ንግግር አትቀበልም ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ ተናግረዋል፡፡

‹‹ እኛ ሳውዲዎች ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል ለመፍታት ተገቢውን እርምጃ እንወስዳለን›› ሲሉ አል- አይባን አፅንኦት ሰጥተው ለተሰብሳቢዎቹ አስረድተዋል፡፡ የሀገሪቱ መስፍኖችም/ ንጉሳውያን የግድያው ፈፃሚዎችን ወደ ፍትህ እያቀረቡ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኃላፊው ንጉሳውያኑ ፍትህን በአለም አቀፍ ህግጋት ተንተርሰው በግልፅነት እንደሚያረጋግጡ አስረድተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሁሉም 28ቱ የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራት እና ሶስት ደርዘን ምዕራባውያን ሀገራት፤ ሳውዲ የግድያውን ጉዳይ ለሚከታተለው የመንግስታቱ ድርጅት አካል ትብብር ማድረግ አለባት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሪያድ ግን አሁንም በግድያው ዙሪያ መረጃ ከማቅረብ የተቆጠበች በመሆኑ፤ ፖለቲከኞች ቱርክ የአለም አቀፉ ማህበረብ፤ በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጫና ማሳደሯን እንድትገፋ እና ያላትንም መረጃ ለአለም አቀፉ የወንጀለኞቸ ፍርድ ቤት አሳልፋ እንደምትሰጥ ያላቸውን እምነት አስታውቀዋል፡፡

የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ከብዙ ጉትጎታ በኋላ ግድያው ላይ ተሳትፈዋል ያሏቸውን 18 ዜጎች፤ ምርመራችንን አጠናቅቀናል ብለው ይፋ ቢያደርጉም፤ የሰዎቹን ዝርዝር ማንነት ግን ግልፅ ከማድረግ ተቆጥበዋል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *