loading
ሳውዲ አረቢያ በውጭ ሀገር ሰራተኞች ላይ የምጥለው ክፈያ የለም አለች፡፡

አርትስ 01/13/2010
የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ሪያድ በውጭ ሀገር ሰራተኞች ወደሀገራቸወ ከሚልኩት ገንዘብ (ሬሚታንስ) ላይ ክፍያ እንዲፈጽሙ ግዴታ ልትጥልባቸው ነው መባሉን የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር አስተባብሏል፡፡
ሚንስቴሩ በሰጠው መግለጫ እየተወራ ያለው አሉባልታ መሰረተ ቢስ ነው፤ ይልቁንም ሀገራችን ነጻ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ትደግፋለች ብሏል፡፡
የመግስት ፍላጎት ሁሉም ሰው በሀገሪቱ ገንዘብ ሲያዘዋውር ህጋዊ መስመሮችን ተከትሎ እንዲሆን እንጂ ማንኛውም ግለሰብ ተጨማሪ ጫና እንዲፈጠርበት አይደለም ብለዋል የሳውዲ ባለስልጣናት፡፡
በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ10 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ሰራተኞች ያሉ ሲሆን ባለፈው ዓመት ብቻ ወደየሀገሮቻቸው በድምሩ 38 ቢሊዮን ዶላር ልከዋል የሚል መረጃ አለ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *