loading
ሪያድ የካሾጊ ገዳዮች የሞት ቅጣት ይገባቸዋል እያለች ነው

ሪያድ የካሾጊ ገዳዮች የሞት ቅጣት ይገባቸዋል እያለች ነው

ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊን በመግደል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የፍርድ ሂደት በትናንትናው ዕለት መሰማት ጀምሯል፤  ሳውዲ አረቢያም በጠቅላይ አቃቢ ህግ በኩል ከተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ በሞት እንዲቀጡ ጠይቃለች፡፡

በመንግስት የሚተዳደረው የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደዘገበው፤ ሪያድ ላይ በዋለው ችሎት አቃቢ ህግ በግድያው ተጠርጥረው በቀረቡት 11 ተከሳሾች ተገቢ ቅጣት እንዲፈርድባቸው የጠየቀ ሲሆን በቀጥታ ከግድያው ጋር የተሳሰሩት አምስት ግለሰቦች ግን ትልቁ የሞት ፍርድ ውሳኔ እንዲበየንባቸው አመልክቷል፡፡

በፍርድ ሂደቱ የመጀመሪያ ቀን የችሎት ውሎ ተከሳሾች፤ ምላሽ ለመስጠት ያመቸን ዘንድ የክስ ማስረጃ ኮፒ እና ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡እንደ የወንጀለኛ መቅጫ  ህግ ደግሞ የተከሳሾች ጥያቄ አግባብነት ያለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ነገር ግን አቃቢ ህግ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሌሎች ግለሰቦች ላይ የሚደረገው ምርመራ መቀጠል እንዳለበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

የሪያድ መንግስትም ለተጨማሪ ማስረጃ ፍለጋ ለቱርክ አቃቢ ህግ ሁለት ደብዳቤዎችን እንደላከ የተነገረ ቢሆንም እስካሁን ግን ምንም ምላሽ እንደልተሰማ ተጠቁሟል፡፡

የቱርክ መንግስት ካሾጊ በአሰቃቂ ሁኔታ በሳውዲ ፍላጎት መገደሉን ለማመልከት እና የሳውዲን ማስመሰል ለማጋለጥ፤ የተቀዳ ድምፅ ለአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያና ጀርመን መላኩን አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *