loading
ሩሲያ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ግዙፉን የጦር ልምምድ ልታደርግ ነው፡፡

 

የሩሲያ የመከላከያ ሚንስትር ሰርጌይ ሾይጎ እንዳሉት ልምምዱ በሚቀጥለው ወር ይጀመራል፡፡

ኢቭኒንግ ስታንዳድ እንደዘገበው ኢስት 2018 የሚል ስያሜ በተሰጠውና በማእከላዊና በምስራቃዊ ሩሲያ በሚካሄደው በዚህ ልምምድ 300 ሽህ ወታደሮች ይሳተፉበታል፡፡

1 ሽህ የጦር አውሮፕላኖች፣ የባህር ሀይል የጦር መርከቦችና የአየር ወለድ ክፍሎችም የወታደራዊ ልምምዱ አካል ናቸው፡፡

የኔቶ አባል ሀገራት በበኩላቸው ከዚህ ግዙፍ ወታደራ ልምምድ ጀርባ ያለው ዓላማ ያሳስበናል በማለት ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ይሁን እንጅ ከሩሲያ ባለስልጣናት በኩል ስልምምዱ ዓላማ የተባለ እስካሁን ነገር የለም፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *