loading
ሩሲያ ቪንዙዌላ ጣልቃ ገብነቷን እንድታቆም አሜሪካን አስጠነቀቀች::

ሩሲያ ቪንዙዌላ ጣልቃ ገብነቷን እንድታቆም አሜሪካን አስጠነቀቀች::

በኒኮላስ ማዱሮ አስተዳደር የተማረሩ  ቪንዙዌላዊያን ለውጥ እንፈልጋለን በማለት ጎዳና ወጥተው ፍላጎታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

ይሄን ተከትሎም ከዋሽንግተን ድጋፍ ያገኙት ተቃዋሚው ጁአን ጉዋይዶ እራሳቸውን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው መሾማቸውን በአደባባይ ተናግረዋል፡፡

የቬንዙዌላ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው ሞስኮ ዋሽንግተን ጣልቃ ገብነቷን ከቀጠለች በውጤቱ ከባድ ጥፋት ይከተላል ብላለች ፡፡

የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ሪያብኮቭ ቬንዙዌላ ስትራጂያዊ አጋራችን በመሆኗ በክፉ ቀን ከጎኗ የመቆም ሀላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው አሜሪካ ኒኮላስ ማዱሮ ከስልጣን እንዲወርዱ የምታደርገው ግፊት በሩሲያ ዓይን ከመፈንቅለ መንግስት   ተለይቶ አይታይም፡፡

ቬንዙዌላዊያን የውስጥ ችግራቸውን በራሳቸው መንገድ እንዲፈቱ ማገዝ እንጂ በሉዓላዊነታቸው ጣልቃ መግባት ህገ ወጥ ተግባር ነው ፤ ስለዚህም አሜሪካ እጇን ትሰብስብ ስትልም አስጠንቅቃለች ሞስኮ፡፡

ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመመረጥ ከሳምንታት በፊት ቅስቀሳ ሲጀምሩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ጁአን ጉዋይዶ ደግሞ ሰሞኑን በደጋፊዎቻቸው ፊት ከእንግዲህ ሀገሪቱን የምመራው እኔ ነኝ ብለው ራሳቸውነ ሾመዋል፡፡

ሞስኮን ያስቆጣው ነገር ጉዋይዶ ይህን በተናገሩ ቅፅበት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በይፋ እውቅና መስጠታቸው ነው፡፡

የአሜሪካን ጣልቃገ ብነት እንደ ቻይና፣ ቱርክ፣ ኩባ፣ ቦሊቪያ እና ሜክሲኮ የመሳሰሉ ሀገራት  ሲቃወሙ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ደግሞ የቬንዙዌላ ህዝብ ለነፃነቱ የሚያደርገው ትግል መደነቅ አለበት ብለዋል፡፡

 

 

ትርጉም በመንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *