loading
ሞቃዲሾ ውስጥ በደረሰ የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ስድስት ሰዎች ሞተዋል፡፡

ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው አጥፍቶ ጠፊወቹ ኬላ ጥሰው በፍጥነት በሚያሽከረከሩበት ወቅት ለማስቆም የሞከሩ ሶስት የጸጥታ ሰራተኞች እና ሌሎች ሶስት ንጹሀን ዜጎች ናቸው በጥቃቱ የተገደሉት፡፡
በአደጋው ሳቢያ ከሞቱት በተጨማሪ 12 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን አንድ ትምህርት ቤት ወደውሟል ነው የተባለው፡፡
የሞቃዲሾ ፖሊስ ሀላፊ ሞሀመድ ሁሴን አጥፍቶ ጠፊወቹ ከዚህም የከፋ ጉዳት የማድረስ እቅድ ነበራቸው ነገር ግን የጸጥታ ሰወቻችን መስዋዕትነት ከፍለው አደጋውን ቀንሰውታል ብለዋል፡፡ 
የአልሸባብ ሀላፊ አብዲያሲስ አቡ ሙሳብ በበኩሉ ድርጊቱን የፈጸመው እርሱ የሚመራው ድርጅት መሆኑንና እስካሁን የሟቾቹ ቁጥር 10 መሆኑን ጭምር በመግለጽ ሀላፊነቱን ወስዷል፡፡
በጥቃቱ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሁለቱ ህጻናት መሆነሰቸውን ዘገባው አክሎ ገልቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *