loading
ምዕመናን የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ ጥሪ መቅረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 በልበ ሙሉነት የልደት በዓልን በቅዱስ ላልይበላ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ ጥሪውን ያስተላለፉት የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ አብያተክርስቲያናትና ገዳማት አስተዳዳሪ አባ ፅጌ ሥላሴ መዝገቡ ናቸው፡፡ አካባቢው በችግር ውስጥ እንደነበር ያስታወሱት አባ ፅጌ ሥላሴ ሁላችንም በከባድ ሐዘን ውስጥ ነበርን፤ አሁን ግን ከወገናችን ጋር በዓሉን በተለመደው መልኩ ለማክበር ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡


የቤተክርስቲያኑ የተለመደው አገልግሎት ሳይጓደል እንደሚፈፀምም ገልፀው ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ የጸጥታ ሥራ መሠራቱንና የየብስና የአየር ትራንስፖርት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል። ልደትን ለማክበር የሚመጡ ሁሉ ማሕደረ ቅርስ የሚባለውን ላስታን ተዘዋውረው እንዲገበኙም ለምዕመናን መልእክት አስተላልፈዋል።


የአካባቢው ማኅበረሰብም መንገድ የጠፋባቸውን በማመላከት፣ የደከሙትን በማሳረፍ፣ እግራቸውን በማጠብ፣ የሚችሉትን ከቤት በማሳረፍ የበረከት ሥራ እንዲሠሩ አሳስበዋል።ከውጭ ሀገር የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን እናውቃለን ያሉት አባ ፅጌ ሥላሴ ስለ ኢትዮጵያ የሚመሰክሩ ጀግኖች ናቸው፤ አሁንም ሀገራቸውን ለማየትና የደረሰውን ጉዳት ለመመልከት የሚመጡ በመሆናቸው ለእነሱ ልዩ የሆነ አቀባበል አለን ነው ያሉት።
ከውጭ ሀገር ለገቡት ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በልዩ ሁኔታ ከሁለት መቶ በላይ አስጎብኚዎች መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *