loading
ምክትል ከንቲባው ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ ይቅርታ ጠየቁ

አርትስ 12/04/2011

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ  ታከለ ኡማ ባለፉት ጊዜያት በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ በግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ላይ ለደረሰው ኢ-ፍትሃዊ ተግባር ይቅርታ ጠየቁ።

ምክትል ከንቲባው በትናንትናው ዕለት ከግብር ከፋይ ነጋዴዎች ባደረጉት ውይይት ነው በነጋዴዎቹ ላይ ደርሶ ለነበረው ኢፍትሃዊ ተግባር ይቅርታ የጠየቁት።

ከአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከመርካቶ እና አካባቢዋ ከተውጣጡ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር በተካሄደው በዚሁ ውይይት  ግብር ከፋይ ነጋዴዎች በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በንግድ ስርአት ህግ፣ በታክስ አሰባሰብ ስርአት ፣በህገ-ወጥ ንግድ እና ተያያዥ  ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ጥያቄ እና ቅሬታ ለከንቲባው አቅርበዋል።

ምክትል ከንቲባው የነጋዴውን ህይወት ለማሻሻል እና የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ ለማድረግ አዲሱ አመራር ጠንክሮ እየሰራነው በማለት ለነጋዴዎቹ ቃል ገብተዋል።

የመርካቶን ግብር ከፋይ መስማት፣ መደገፍ እና ማብቃት የከተማዋን እድገት ማፋጠን ነው ያሉት ታከለ ኡማ ፣ ፍትሃዊየንግድ ስርአት ለመፍጠር የከተማው አስተዳደር በቅርብ ቀን አዳዲስ አሰራሮችን ለህዝብ ይፋ ያደርጋል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *