loading
ምክትል ከንቲባው በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደርን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

ምክትል ከንቲባው በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደርን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

አርትስ 21/02/2011

 

ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ ከአምባሳደር ሱዛና ሙርሔድ ጋር በነበራቸው ቆይታ  በትምህርት፣ ትራንስፖርት ፣ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል በሚቻልበትፕሮጀክት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

እንዲሁም አዲስ አበባን ልዩ የቱሪዝም መዳረሻ ከተማ ለማድረግ በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ዙሪያ በተለይም የእንጦጦ ተፋሰሶችን ተከትሎ እየተሰራ ባለው የአረንጓዴ ፕሮጀክት የህዝብ መዝናኛና ሌሎችየከተማዋ ጉዳዮች ላይ በጋራ ስለሚሰሩበት መንገድ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል ተብሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እንደገለጸዉ አምባሳደር ሱዛና ሙርሔድ አሁን በሀገሪቱ ያለውን ለውጥ እንደሚያደንቁና ያለው ለውጥ በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ተነሣሽነት እንደፈጠረላቸውምገልፀዋል፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *