loading
ማንችስተር ሲቲ ወደ ደረጃ ሰንጠራዡ አናት ለመመለስ እያለመ ዛሬ የሊግ ጨዋታውን ያደረጋል

ማንችስተር ሲቲ ወደ ደረጃ ሰንጠራዡ አናት ለመመለስ እያለመ ዛሬ የሊግ ጨዋታውን ያደረጋል

 

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት አንድ ግጥሚያ ዛሬ ምሽት ይከናወናል፤ ጨዋታው በመርሲ ሳይድ፤ በኢቨርተን እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ላይ ይከናወናል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ በጣፋጮቹ በኩል የማርኮ ሲልቫ ቀዳሚ ተመራጭ ሉካስ ዲኜ ከቅጣት ተመልሶ አገልግሎት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ የቡድኑ ቁልፍ አማካይ ተጫዋች ኢድሪሳ ጉዬ ከጉዳት ሲመለስ ዬሪ ሚና፣ ሌይተን ቤንስ እና ፊል ጃጌልካ በጉዳት ለኢቨርተን አይሰለፉም ተብሏል፡፡

የማንችስተር ሲቲው ተመላላሽ ተጫዋች ቤንጃን ሜንዲ ከጉዳት መልስ ሊኖር እንደሚችል ሲጠቆም ተከላካዩ ቪንሰንት ካምፓኒ በጡንቻ ጉዳት ከፍልሚያው ውጭ ነው፡፡

የኢቨርተን አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ‹‹ጨዋታዎቹን ስታሸንፍ ሰዎች ጥሩ ነው ይላሉ፤ ሳታሸንፍ ስትቀር ደግሞ ሁኔታው ኖርማል ነው›› ብለዋል፡፡ ሲልቫ ጥሩ ቡድን እየገነቡ ቢሆንም እያጋጠማቸው ካለ ደካማ ውጤት አንፃር ስራቸው ስጋት ላይ እንደሚገኝ መገናኛ ብዙሀኑ እየዘገቡ ነው፡፡

የሲቲው ፔፕ ጓርዲዮላ ደግሞ ‹‹ ከሶስት እና አራት ቀናት በፊት ሁላችንም የሊጉን ሻምፒዮንነት ለሊቨርፑል ነበር የሰጠነው፤ አሁን ደግሞ እኛ ተመራጭ ሁነናል፤ ምናልባትም በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት እኛ መሪ ልንሆን እንችላለን አሊያ በስድስት ነጥብ ልናንስ እንችላለን፤ ሁኔታውን ለማረጋጋት እንሞክራለን›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ኢቨርተን ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባደረጋቸው 11 የመጨረሻ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች፤ ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ሲሆን ይህም በ2017 ጉዲሰን ፓርክ ላይ 4 ለ 0 መርታቱ ይታወሳል፡፡ የመርሲ ሳይዱ ክለብ ባለፉት 12 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሶስቱን ብቻ ሲያሸንፍ፤ በሰባቱ ተረትቷል፡፡

በዛሬው ምሽት ፍልሚያ የጓርዲዮላ ቡድን የሚያሸንፍ ከሆነ የሊጉን መሪነት በግብ በመብለጥ ከቀያዮቹ የሚረከብ ይሆናል፡፡ ጣፋጮቹ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ደግሞ ነጥባቸውን ወደ 37 ከፍ በማድረግ 8ኛ ደረጃን ይቆናጠጣሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *