loading
ማህበሩ የገናን በዓል አስመልክቶ ለ600 የኩላሊት ህመምተኞች ነጻ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ሊሰጥ ነው

ለኩላሊት ህመምተኞች ነጻ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ሊሰጥ ነው።

 

የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ማህበር ይህንን ድጋፍ የሚያደርገው   የኩላሊት እጥበት በሚያካሂዱ የግልና የመንግስት ተቋማት ውስጥ አገልግሎቱን በመጠቀም ላይ ላሉ  ህመምተኞች ነው።

 

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ ህመምተኞች ከክፍያ ነጻ አገልግሎት እንዲያገኙ 600ሺህ ብር መድቦ የአንድ ቀን የኩላሊት እጥበት ወጪያቸውን ለመሸፈን ተዘጋጅቷል።

 

ድጋፉ እስከገና በዓል ድረስ ህክምናውን ለሚከታተሉ ህመምተኞች ይሰጣል ያሉት አቶ ሰለሞን የዚህ ፕሮግራም አላማ ህመምተኞቹ ለአንድ ቀን ለኩላሊት እጥበት ሊያወጡት የነበረውን 1500 ብር ለበዓል መዋያ እንዲያውሉት በማድረግ አጋርነታችን መግለጽ ነው ብለዋል።

 

እንደስራ አስኪያጁ ገለጻ ማህበሩ የኩላሊት እጥበት ከክፍያ ነጻ እንዲሆን ለማድረግ ከ17 ባንኮች ጋር በጥምረት እየሰራ ይገኛል።

 

የኩላሊት እጥበት ህመምተኞች በየመንገዱ ምጽዋት የሚጠይቁበት ጊዜ እንዲያከትም ለማድረግ ማህበራችን ጠንካራ ስራዎችን በማከናወን ላይ ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ መላው ህብረተሰብ ይህንን ዓላማ በመደገፍና የህመምተኞቹን ስቃይ በመቀነስ የበኩሉን እንዲወጣ እንጠይቃለን ብለዋል።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *