ሚኒስቴሩ ከ350 በላይ ለሆኑ በውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛን አገናኝ ኤጀንሲዎች ፍቃድ ሰጠ፡፡
ሚኒስቴሩ ከ350 በላይ ለሆኑ በውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛን አገናኝ ኤጀንሲዎች ፍቃድ ሰጠ፡፡
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛን ለሚያገናኙ ከ350 በላይ ኤጀንሲዎች ህጋዊ ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል፡፡
በቅርቡ የሁለትዮሽ ስምምነት ወደተደረገባቸው ሀገራት የስራ ስምሪት የሚያደርጉ ዜጎች ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ህጋዊ ፈቃድ ያገኙ ኤጀንሲዎችን ብቻ በመጠቀም እራሳቸውን ከህገ ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች መጠበቅ እንዳለባቸው ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሁለትሽ ስምምነቱ ውደ ተደረገባቸው ሃገራት የሚጓዙ ዜጎች ህጋዊ መንገድን ብቻ እንዲከተሉ ሚኒስቴር መስረያቤቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡