ሙስና ኢትዮጵያን በአስር ዓመት ውስጥ ብቻ 7 ቢሊየን ዶላር አሳጥቷታል ተባለ
ሙስና ኢትዮጵያን በአስር ዓመት ውስጥ ብቻ 7 ቢሊየን ዶላር አሳጥቷታል ተባለ
አርትስ 05/04/2011
በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት በተካሄደውና “ሁለንተናዊ ልማታችንና ሰላማችንን ለማረጋገጥ በሙስና ላይ እንዝመት፣ ጊዜው የተግባር ነው”’ በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚሁ በዓል ላይ ሙስና በህዝቦች ልማት፣ ሰላምና አንድነት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።
ሆኖም ይህ ጉዳት እየታወቀ ችግሩን ለመከላከል የተሰጠው ትኩረትና ሙስናን ከስሩ ለማድረቅ እየተሰራ ያለው ስራ አነስተኛ መሆኑም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
ችግሩን ለመከላከል በሃገሪቱ በየጊዜው የሚረቀቁ ህጎች አመርቂ ውጤት አለማስገኘታቸውም በመድረኩ ላይ በውይይት መድረኩ ላይ ተገልጿል።
የሃገራችንን ልማትና ሰላም ለማረጋገጥ የዴሞክራሲ፣ የፍትህ እና የዴሞክራሲ ተቋማትን በፅኑ መሰረት ላይ መገንባት ያስፈልጋል ተብሏል።
በውይይቱ እንደተገለጸው ሙስናና ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊቶች በሂደት እየከሰሙ የሚሄዱበትን ዘላቂ አሰራር ለመተግበር አማራጩም ይው ብቻ ነው ።
ለዚህም እያንዳንዱ ዜጋ ሙስናን በመፀየፍ፣ ልማትን በመደገፍ እና ብልሹ አሰራሮችን በማጋለጥ ለተጀመረው ለውጥ አጋዥ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።