loading
ሙሀማዱ ቡሀሪ እመኑኝ አልሞትኩም እያሉ ነው

ሙሀማዱ ቡሀሪ እመኑኝ አልሞትኩም እያሉ ነው

አርትስ 24/03/2011

በርካታ ናይጀሪያውን ፕሬዝዳንት ሙሀመዱ ቡሃሪ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት በጠና ታመው ለህክምና ለንደን ሲመላለሱ ከቆዩ በኋላ በህይወት አሉ ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሰሞኑን ወደ ፖላንድ ተጉዘው የናይጀሪያ ኮሚዩኒሚቲ ኣባላት ጋር ባደረጉት ውይይት እኔ አልሞትኩም ይሄው ከፊታችሁ የቆመው እውነተኛው ቡሃሪ ነው ብለዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ከሞቱ በኋላ  ጁብሪል አል ሱዳኒ የተባለ ግለሰብ  ከሱዳን ተፈልጎ መጥቶ ናይጀሪያን እያስተዳደረ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡

አንዳንዶቹ ደግሞ ክሎኒንግ በተባለው ሳይንስ ቡሀሪ ተመሳሳይ ሰው ተፈጥሮላቸው እንዳሉ ተደርጎ ይነገራል እንጂ እሳቸው በህይት የሉም የሚል እምነት አላቸው፡፡

እሳቸው ግን በጠያቂወቻቸው ፊት ቀርበው ብዙ ሰዎች ይህን አሉባልታ ያናፍሳሉ አኔ ግን ይሄው ከፊታችሁ ቆሜያለሁ፡፡ በቅርቡ 76ኛ ዓመቴን ለማክበር ተዘጋጅቻለሁ ፍፁም ጥንካሬም ይሰማኛል በለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *