loading
መንግስት የህዝቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉና ህገመንግስቱን የሚጥሱ አካላትን አልታገስም አለ

መንግስት የህዝቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉና ህገመንግስቱን የሚጥሱ አካላትን አልታገስም አለ

አርትስ 20/02/2011

ሰሞኑን በምእራብ ኦሮሚያ ዞኖችና በቄለም ወለጋ በኦነግ ስም በመታጠቅ ህዝቡን ለችግር እየዳረገ ያለ አካል በአፋጣኝ ከዚህ ተግባር እንዲታቀብ አቶ ለማ መገርሳ አሳሰቡ።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ  እንደተናገሩት መንግስት እስካሁን እንዲህ አይነቱን ተግባር በትዕግስት ሲመለከት ነበር ብለዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ግን መንግስት የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ እና ህገ መንግስቱን ለማስከበር እንደሚሰራ  ተናግረዋል።

በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ እና እጃቸው ያለበት ሰዎች ይህን ተግባራቸውን እንዲያቆሙ ህብረተሰቡ እና የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ በማቅረብ ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ ለማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ዛሬ በማህበራዊ  ገፁ ባሰፈረው መግለጫ እንዳለው በክልሉ እየደረሰ ላለው ጉዳት ሃላፊነት የሚወሰድ አካል ሊታወቅ ይገባል፤ መንግስትም ለዜጎች ተገቢውን ጥበቃ ማድረገና በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የማስቆም ሀላፊነት አለበት ብሏል፡፡ በስሙ እየተንቀሳቀሱ ነው ስለሚባሉት ሃይሎች ግን ኦነግ በመግለጫው  ያለው ነገር የለም፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *