ሐሰት፡ ይህ ምስል የህወሓት አማጽያን አንዋጋም ያሉትን ወጣቶች ሲረሽኑ አያሳይም።
ምስሉ የባንግላዲሽ ወታደሮች ከባድ ስልጠና ሲሰለጥኑ ያሳያል።
ጁንታው (ህወሓት) አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ወጣቶችን ረሸናቸው በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ምስል ሐሰተኛ ነው።
በልጥፉ ላይ በአማርኛ ቋንቋ የተጻፈው ጽሁፍ “ጁንታው አንዋጋም ያሉትን ወጣቶችን እረሸናቸው።እግዚኦ ! የትግራይ ወጣቶች አለቁ” ይላል፡፡
የያንዴክስ የምስል ፍለጋ (Yandex image search) ውጤት እንደሚያሳየው ይህ ምስል እ.ኤ.አ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ከተለቀቀው የዩትዩብ ቪዲዮ ልባስ (Thumbnail) የተወሰደ ሲሆን ምስሉ በቪዲዮው 01፡13ተኛ ደቂቃ ላይ ይገኛል።
በቪዲዮው ላይ የባንግላዴሽ ወታደራዊ አካዳሚ ለባንግላዴሽ ጦር ሠራዊቶች አካላዊና አዕምሮአዊ ፅናት ለማጎልበት ያሰበ ከባድ ሥልጠና ሲያሰለጥን ያሳያል።
ይህ ምስል በልጥፉ ላይ የህወሓት አማጺያን አድርገውታል የተባለውን ድርጊትን ባይገልጽም አማጺው በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች ንጹሃኖችን መግደሉን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ጦርነቱ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በመስፋፋቱ አካባቢዎቹን የተቆጣጠሩት የህወሓት አማጺያን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
በማይካድራም የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ ንፁሃን ዜጎችን ህወሓት እንደገደለ የተባበሩት መንግሥታት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያካሄዱት ጥናት ገልጿል።
አርትስ ቲቪ ጁንታው (ህወሓት) አንዋጋም ያሉትን የትግራይ ወጣቶችን እረሸናቸው በሚል የተለጠፈው የፌስቡክ ምስል ተመልክቶ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
. . . . .
ይህ ልጥፍ በፌስቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የፔሳቼክ የእውነታ መርማሪዎች በተከታታይ የሚያደርጉት የመረጃ ማረጋገጥ እና የተሳሳተ መረጃን የማጋለጥ ተግባር አካል ነው::
እንደ ፔሳቼክ ያሉ ገለልተኛ ሶስተኛ ወገን የእውነት መርማሪ ድርጅቶች ከፌስቡክ እና የማህበራዊ ድረ ገጾች ጋር በመጣመር የሃሰት ዜናን መለየት እንዲያስችልዎ ይሰራሉ:: ይህን የምናደርገውም በየማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የሚመለከቱት ልጥፍ/ መረጃ መነሻቸውን በማያያዝ እና ጠለቅ ያለ ዕይታ እንዲኖርዎ በማድረግ ነው::
በፌስ ቡክ ላይ የሐሰተኛ መረጃ ወይም የተጭበረበረ የመሰልዎ አጋጣሚ አለ?እንግድያውስ በእዚህ መንገድ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ::እንዲሁም ይህን ተጨማሪ ኢንፎርሜሽን በመጠቀም አጠራጣሪ መልዕክቶችን ለመለየት የፔሳቼክ መንገዶችን ማየት ይችላሉ::
ይህ የእውነታ ምርመራ በአርትስ ቲቪ የእውነት መርማሪ ረደኤት አበራ ተጽፎ በፔሳቼክ ም/አዘጋጅ ኤደን ብርሃኔ አርትኦት የቀረበ ነው::
አንቀጹ ለህትመት እንዲበቃ ያረጋገጠው ደግሞ የፔሳቼክ ዋ/አዘጋጅ ኤኖክ ናያርኪ ነው::
ፔሳቼክ የምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የፋይናንስ መረጃ መርማሪ ተቋም ነው :: ካትሪን ጊቼሩ እና ጀስቲን አርንስቴን በተባሉ ሰዎች የተመሰረተ እንዲሁም በአህጉሪቱ ትልቁ የሲቪክ ቴክኖሎጂ እና የጋዜጠኝነት መረጃ ቋት አቅራቢ በኮድ አፍሪካ የተገነባ ነው:: እንደ ጤና : የገጠር ልማት እና የንጹህ ውሃ አቅርቦት በመሳሰሉ መስኮች ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከመንግስት የሚጠበቁ አቅርቦቶች ላይ የተጨባጩን ዓለም እይታችንን ሊቀርጹ የሚችሉ በይፋ በሚሰራጩ የፋይናንንስ መረጃዎችን ዙርያ ህብረተሰቡ እውነተኛ መረጃን ማገናዘብ እንዲችል ለማገዝ የሚያስችል ድጋፍ ይሰጣል:: ፔሳቼክ ሚድያዎች የሚያቀርቡትን ጥንቅርም ይፈትናል:: የበለጠ መረጃ ለማግኘት pesacheck.org. ይጎብኙ::
ፔሳቼክ ኮድ ፎር አፍሪካ ከዶቼቬለ አካዳሚያ ባገኘው ድጋፍ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሚድያዎች እንዲሁም የሲቪክ ተቋማት ጋር በመተባበር ኢኖቬት አፍሪካ ፈንድ በሚለው መስመሩ የሚያቀርበው እንቅስቃሴ ነው::