loading
ላል ይበላ የኛ ብቻ ሳይሆን የዓለም ፤ የአፍሪካም ቅርስ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ላል ይበላ የኛ ብቻ ሳይሆን የዓለም ፤ የአፍሪካም ቅርስ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

አርትስ 18/02/2011
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የላልይበላ  ውቅር አብያተ-ክርስቲያናት ጥበቃና ጥገና የሚያገኙበትን ሁኔታ ተዘዋውረው  ጎብኝተዋል::
የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ እንዳስታወቁት በቅድሚያም ቤተ-መድሃኒዓለም ሲጎበኝ በድንገት ለተሰበሰበው የከተማው ህዝብ ንግግር ያደረጉት  ጠቅላይ ሚንስትሩ “ላል ይበላን የሚያክል ድንቅ የዓለምና የአፍሪካ ቅርስ ፤ ለእኛ ደግሞ ከዚያም በላይ መኩሪያችንና መመኪያችንን ስለሆነ ደግመን መገንባት ባንችልም እንኳ መጠበቅ ግን ግዴታችን ነው” ብለዋል::
ዛሬ በአማራ ክልል ሰልፈኞች ሲሰሙ የነበሩ ጥያቄዎች የላልይበላን እና የጣናን ጉዳይ የተመለከቱ ሲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ቡድን ሁለቱንም ጎብኝቷል።
ትናንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን 20ሚሊዮን ብር ቃል መግባቷ ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *