ለገና ዋዜማ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጎበኙት እማማ ዘውዲቱ ምስጋና አቀረቡ፡፡
ለገና ዋዜማ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጎበኙት እማማ ዘውዲቱ
ምስጋና አቀረቡ፡፡
የእማማ ዘዉዲቱ በጎአድራጎት ማህብር ከሳምንት በፊት የጎበኘዉ አርትስ ቲቪ የእማማ ዘዉዲቱን ኑና ጎበኙን ለበአል አብረን እናክብር ብለዉ ጥሪ አቅርበዉ ነበር፡፡በዋዜማዉም በጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤታቸዉ ተጎብኝተዋል፡፡
እማማ ዘዉዲቱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በተመለከት በስልክ ስናናግራቸዉ የተሰማቸውን ደስታ እንባ እየተናነቃቸው ነግረውናል ፣
እማማ እንዲህ አሉ .. ልጆቹ አለሁላችሁ የሚላቸው ወገን ነው የሚፈልጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለባለቤታቸው እድሜ ይስጣቸው፣ በእሳት አደጋው ምክንያት ያጡትን የትምህርት ቁሳቁስ እና ብርድ ልብስ አምጥተውላቸዋል፡፡ ሌላ ምንም አልልም እኛን ፣ እነዚህን ህጻናት ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ባለቤታቸውን እድሜ ይስጥልን ሲሉ እማማ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ከሳምንት በፊት ያቀረብነዉ ዘገባችን ይኸዉ፡፡ሰላም ገብሩ አዘጋጅታዋለች፡፡