loading
ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና አንድነት እንዲበጅ ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ፣ጸሎትና ምህላ ታወጀ፡፡

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ አባቶች እና የኢትዮጵያ የሀገር ሽማግሌዎች አሁን በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ በተመለከተ መልዕክት ካስተላልፉ በኋላ ነዉ የጾምና፤የጸሎት ና ምህላ የታወጀ

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ አቶ መስኡድ አደም ለአርትስ ቲቨ እንደተናገሩት በጉባኤዉ የሀይማኖት አባቶቹ  የወገኖቻችን ሞት፣ መፈናቀልና ጉዳት በአፋጣኝ በማቆም ሁሉም ወገን ቅድሚያ ለሀገራዊ አንድነት ፣ለሰብአዊ ክብርናሰላም ሊተጋ ይገባል ሲሉ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በኋላም በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ ምንም አይነት ግጭት እና የሚተኮስ ጥይት ሊኖር እንደማይገባም አሳስበው፤የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ  አባላት በጋራ በመሆን ለመላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ባለአስር ነጥብ የሰላም መልዕክት እናየተማጽዕኖ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ግጭቱ ተወግዶ የታሰበው ሰላም እውን እንዲሆንም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አማኞች በሙሉ እንደየ ዕምነታቸው ለሁለት ወራት የሚዘልቅ ጾም ጸሎትና ምሕላ ታውጇል ፡፡

ምህላዉ ሁሉም ቤተ እምነቶች ለሁለት ወር የሚያካሄዱት ሲሆን በራሳቸዉ ፕሮግራም ይመራሉ ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *