loading
ለአባጅፋር ቤተመንግስት እድሳት ወደ 8 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተመደበ

አርትስ 19/02/2011

ገንዘቡ  ከቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከአሜሪካ ኤምባሲም በጋራ  የተመደበ ነዉ፡፡

በቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፋንታ በየነ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቅርሶችን በመንከባከብለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ዓመትም የአክሱም ሀውልት ከሮም ሲመለስ የታሰረበትን ገመድ የመፍታት እና የማጠናከር፣ ለፋሲል ግንብና ለላሊይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት እና በጎሬ ለሚገኘው ታሪካዊው የእንግሊዝ ቆንስላን ጨምሮ ለተለያዩ ቅርሶች እድሳት ይደረጋል ብለዋል።

በየጊዜው ቅርሶቹን አድሶ ከሚጋረጥባቸው አደጋ ለመከላከል የበጀትና የባለሙያ እጥረት እንቅፋት መሆኑን አቶ ፋንታ ይናገራሉ።

አሁን ላይም በመስኩ የሚያጋጥመውን የሰው ሀይል ለማፍራት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን፥ በሀገሪቱ በሚገኙከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል ባለሙያዎችን የማሰልጠን ስራ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

ፋና እንደዘገበዉ  አቶ ፋንታ ቅርሶቹ አደጋ ሳይጋረጥባቸው ቀድሞ የማደሱ ተግባር በመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በቅንጅት መስራትቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *