loading
ለህግ ታራሚዎች የተደረገ ይቅርታ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የአማራ ክልል ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ገለጸ የአማራ ክልላዊ መንግስት ለ2ሺህ 705 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለምሸት ምህረቴ ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ለታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው በይቅርታ ቦርዱ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ሁለት ሶስተኛውን የእስር ጊዜ የጨረሱ፣ በፈፀሙት ወንጀል የተፀፀቱ፣ በዕድሜ የገፉና ከህፃናት ልጆች ጋር የታሰሩ ይገኙበታል። የአስገድዶ መድፈር፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የሙስና፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሌሎች በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ወንጀሎችን ፈፅመው የታሰሩ ታራሚዎችን ይቅርታው እንደማያካትትም አመልክተዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት ታራሚዎች መካከልም 56 ሴቶች መሆናቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎችም ከዛሬ ጀምሮ ከያሉበት ማረሚያ ቤት እንዲወጡ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎችም ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ያሳዩትን መልካም ስነምግባር ለበደሉት ህብረተሰብ በልማት ሊክሱት እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ ህብረተሰቡም ታራሚዎቹ በፈፀሙት ወንጀል የተፀፀቱ በመሆናቸው ሳያገላቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባም አቶ አለምሸት አመልክተዋል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *