loading
ህገ መንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ህገ መንግሰታዊ መብታችን ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

በዛሬው ዕለት በሲዳማ ዞን በሚገኙ 36 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድሮች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉበት ያለው ሰላማዊ ሰልፍ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄን በህገ መንግስቱ መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ ነው ተብሏል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች “ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር ! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል።

ጥዋት ላይ መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻውን ሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲዮም ላይ በማድረግ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት በጥቅምት ወር ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ሂደቱን ተከትሎ እንዲፈጸም ባለፈው ጥቅምት ወር ባካሄደው ጉባኤ መወሰኑ ይታወሳል።

ምንጭ ፤-ፋና

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *