loading
ሁለቱ ኮሪያዎች ፍቅራቸው ፀንቷል፡፡

አርትስ 01/13/2010
ለዓመታት የጎሪጥ ሲተያዩ የኖሩት ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ አሁን በመካላቸው የሰላም አየር መንፈስ ከጀመረ ውሎ አድሯል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች በፈረንጆቹ መስከረም 18 በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ ተገናኝተው ሊወያዩ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን እና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው ኪም ጆንግ ኡን ፒዮንግያንግ ሲገናኙ ቀጠናውን ከኒውክሌር ነፃ ስለማድረግ ይመክራሉ ነው የተባለው፡፡
ፕሬዝዳንት ኪም ለአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ የገቡላቸው የኒውክሌር ተቋሞቻቸውን የማፍረስ ተግባር እንደማይቀየር ለደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ነግረዋቸዋልም ተብሏል፡፡
ዋሽንግተን ፒዮንግያንግ ከሲንጋፖሩ ስብሰባ በኋላ በቃሏ አልተገኘችም በማለት ተደጋጋሚ ወቀሳ ስታሰማ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *