loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በያዝነው ወር መጨረሻ በቻይና ጉብኝት ያደርጋሉ::
በቆይታቸውም ከፈረንጆቹ መስከረም 3 እስከ 4 ድረስ በቤጂንግ በሚካሄደው በቻይና አፍሪካ ፎረም ላይ እንደሚሳተፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።
ከፎረሙ ጎን ለጎንም ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪ ኪያንግ ጋር ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
እንደ ፅህፈት ቤት ሀላፊው ገለፃ ቻይና ቀዳሚዋ የኢትዮጵያ የንግድ አጋር እና የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ምንጭ ናት።
ፋና እንደዘገበዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *