የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንድነት ላይ ያተኮሩ በዓላትን ላዘጋጅ ነዉ አለ፡፡
ከነሐሴ አጋማሽ አስከ መስከረም 30 የሚቆየዉ የበዓላት ዝግጅት “አንድ ሆነን አንድ እንበል” በሚል መሪቃል የሚከበር ነዉ፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሚዘጋጁት የተለያዩ በዓላት ለአዲስ አመት የሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ቱሪስቶችን መቀበል ላይ ያተኮረ ነዉ ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ በሆቴሎች በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በአስጎብኚ ድርጅቶች ያገልግሎት ዋጋ ቅነሳ በተጨማሪ ሁላችንም ኢትዮጵያዉን ፤ኢትዮጵያዊ በሆነ የእንግዳ አቀባበል ባህላችን የአዲስ አመት እንግዶቻችን እንቀበል ብለዋል፡፡
በተያያዘም ከፊታችን አርብ ጀምሮ ከኤርትራዊያን ጋር የባህል ልምድ ልዉዉጥ በባህል ማዕከል ለማድረግ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ ብሏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ነሐሴ 18 የባህል ኤግዚቢሽን እንደሚከፍትም ሰምተናል፡፡