loading
ከ 10 የዓለማችን የተበከሉ ከተሞች ዉስጥ ሰባቱ የህንድ ከተሞች መሆናቸዉን አንድ ጥናት አመለከተ

ከ 10 የዓለማችን የተበከሉ ከተሞች ዉስጥ ሰባቱ የህንድ ከተሞች መሆናቸዉን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

መቀመጫዉን በኢዥያ ያደረገዉ ኤር ቪዥዋል ኤንድ ግሪን ፒስ የተሰኘዉ ተቋም ባወጣዉ ጥናት  ከተበከሉ የዓለማችን ከተሞችም 50ዎቹ የሚገኙት  በህንድ በፓኪስታን በባንግላዲሽና በቻይና መሆኑን አመልክቷል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በህንድ ከኒዉደልሂ ደቡባዊ ምዕራብ 30 ኪሎሜትር ላይ  የምትገኘዉ ጉርጉራም የተባለችው ከተማ የዓለማችን አንደኛዋ የተበከለች ከተማ  ሆናለች፡፡

ሶስቱ ሌሎች የህንድ ከተሞችና የፓኪስታንዋ ፌሳላባድ ከ5ቱ የተበከሉ ከተሞች ዝርዝር ዉስጥ ተካትተዋል፡፡

ከ20 ዎቹ የአለማችን የተበከሉ ከተሞች ዉስጥ ደግሞ 18ቱ በህንድ ባንግላዲሽና ፓኪስታን ዉስጥ የሚገኙ ናቸዉ ይላል ጥናቱ፡፡

ጥናቱን ያካሄደዉ ተቋም ሀላፊ የብ ሳኖ በከተሞች ብክለት ምክንያት ዓለማችን 225 ቢለዮን ዶላር የሚያወጣ ኪሳራ ደርሶባታል ለህክምና የሚወጣዉም ወጪ  ትሪሊየን ዶላር ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡ የዚህ ጥናት ዉጤትም አለም አሁንም ለአየር ብክለት ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠዉ የሚያሳስብ ነዉ ተብሏል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *