አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ
አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ።
ባለቤትነቱ የኤር ዚምባብዌ የሆነ ቦይንግ-ሰራሽ የቦይንግ 767-200ኤር አውሮፕላን ነው ሞተሩ በሚገኝበት የአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት የፈጠረው፡፡
ይህ አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ ከተነሳ በኋላ ነው ብልሽቱ እና የእሳት ብልጭታው የታየው ሲል የሃገሪቱ አየር መንገድ ያስታወቀው፡፡
በብልሽቱ በረራው አለመስተጓጉሉና አውሮፕላኑ ሀራሬ በሰላም ደርሶ ማረፉን ኤር ዚምባብዌ ገልጿል፡፡
የዙምባቡዌ አየር መንገድ የብልሽቱን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል፡