loading
አቡዳቢ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትዘረጋ ነው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሪም አል ሃሺሚ አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተው በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሚድል ኢስት ሞኒተር የኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎችን ጠቅሶ እንደዘገበው የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሩ ከአዲስ አበባ አሰብ ይዘረጋል ።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አርጋ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከአቡዳቢ ጋር የተደረገው ውይይት በኢንቨስትመንት፣በግብርናና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።

አል ሃሺሚ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ከተወያዩ በኋላ ሃገራቸው በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ በመጠቀም በጋራ መስራት እንደምትፈልግ ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *