loading
ቡሀሪ ምርጫው ለምን እንደተራዘመ ይጣራልኝ አሉ፡፡

ቡሀሪ ምርጫው ለምን እንደተራዘመ ይጣራልኝ አሉ፡፡

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡሀሪ ባለፈው ቅዳሜ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መራዘሙ

ጥርጣሬ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ የትራንስፖርት እና መሰል እጥረት ችግሮች ገጥመውኝ ነው ለሳምንት ያተላለፍኩት ብሏል፡፡

ቡሀሪ ከፓርቲያቸው ሰዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ እንዳሉት የምርጫ አስፈፃሚዎቹ በተለይ ምርጫው ሊካሄድ ሰዓታት ብቻ ሲቀረው ተሰርዟል ማለታቸውን አልወደዱትም፡፡

እንዲህ ማድረግ እንደሚቻልም እርግጠኛ አይደለሁም ያሉት ፕሬዝዳንቱ እንዲህ አይነቱ ስራ ለህዝቡ በይፋ ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል ነው ያሉት፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ቡሀሪ ለአንድ ሳምንት የተራዘመው ምርጫ እንዳለቀ ቀጣዩ ስራችን የሚሆነው ለምን አሳማኝ ባልሆ ምክንያት ምርጫው እንደተራዘመ እና ለዚህም ማን ሀላፊነቱን እንደሚወስድ ማጣራት ይሆናል ብዋል፡፡

ባፈው ሳምንት መንግስት እና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከውጤት በኋላ ብጥብጥ እንዳይነሳ የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *