በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰ
በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰ
ኪዳል ከተባለችው የማሊ ክልል በ200 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ካምፕ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በጥቃቱ 10 የቻድ ወታደሮች ህይዎታቸው ሲያልፍ ሌሎች 25 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል፡፡
የመንግታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በረቀቀ መንገድ ጥቃቱን ያደረሱት አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብለዋል፡፡
አልቃኢዳ ኢን ኢስላሚክ መግረብ የተሰኘው ቡድን ጥቃቱን ያደረስኩት እኔ ነኝ በማለት ሀላፊነቱን መውሰዱን የሞሪታኒያው አል አክባር የዜና ወኪል በዘገባው አስነብቧል፡፡
ቡድኑ ይህን ጥቃት ለማድረስ ምክንያት የሆነውም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለጉብኝት ቻድ መግባታቸው መሆኑን ቡድኑ ይፋ አድርጓል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማሊ 1 ሺህ 200 የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ያሰማራ ሲሆን ሀገሪቱ ለሰላም አስከባሪ ሀይሎች እጅግ አደገኛ ከሚባሉት ሀገራ በቀዳሚነት ትገኛለች፡፡
ምክንያቱ ደግሞ ማሊ ውስጥ አልቃኢዳ እና አይ ኤስ አይ ኤስን ጨምሮ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች በስፋት የሚገኙ መሆናቸው ነው፡፡