loading
ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች መርማሪዎቼ መንቀሳቀስ አልቻሉም አለ

አርትስ 23/01/2011
የመልካም አስተዳደርና የማንነት ጥያቄን መንግስት በአፋጣኝ መፍታት አለበት ያሉት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ግጭት ከተከሰተባቸውና አሁንም ችግሩ አሳሳቢ በሆነባቸው በቤኒሻንጉል ከማሺ እንዲሁም በደቡብ ሸካና ከፋ ዞኖች ኮሚሽኑ መርማሪዎችን ቢልክም በስፍራው ያለው አለመረጋጋት ስራቸውን እንዳይሰሩ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
ዛሬ ከተለያዩ አመራሮች ጋር ባደረግነው ውይይት በነገው እለት ተሰማርተው ስለደረሰው ጉዳት መረጃ ይሰበስባሉ ብለዋል።
የተጎጂዎችን ቁጥር ከምርመራው በኋላ እናሳውቃለን ያሉት ኮሚሽነሩ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ከሚደረገው እንቅስቃሴ ይልቅ ኮሚሽኑ በየጊዜው ችግሮችን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥናቶችን ለመንግስት እንደሚያቀርብ ገልፀዋል። ይህም አሁን የሚያጋጥሙትንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ብለዋል። ከነዚህም መካከል በ2009 ዓ.ም እና በ2010ዓ.ም የቀረቡትን ጠቅሰዋል።
ከግጭት በኋላ ኮሚሽኑ የሚያደርገው ምርመራ ተጠያቂዎች ለህግ እንዲቀርቡና የህግ የበላይነት እንዲከበር ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል። አሁን በተለያዩ ቦታዎች እያጋጠመ ላለው ችግር የፀጥታ ሀይሉ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *