loading
ማንችስተር ሲቲና ቶተንሃም ከሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት አጥብበዋል

ማንችስተር ሲቲና ቶተንሃም ከሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት አጥብበዋል

የ23ኛ ሳምንት መርሃግብር የመጨረሻ ጨዋታዎች በትናንትናው ዕለት ሲከናወኑ፤ የፔፕ ጓርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ወደ ጆን ስሚዝ ስታዲየም አቅንቶ አሰልጣኝ ዴቪድ ዋግነርን ያሰናበተውን ሀደርስፊልድ ታውን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ድል አድርጎ ተመልሷል፤ ቅዳሜ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ወደ ሰባት ከፍ ብሎ የነበረውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አራት መልሶታል፡፡

ተከላካዩ ዳኒሎ የውሃ ሰማያዊዎቹን ቀዳሚ ግብ ከመረብ ሲያገናኝ፤   ሊሮይ ሳኔ እና ራሂም ስተርሊንግ ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ወደ ክራቨን ኮቴጅ ያቀናው ቶተንሃም ሆትስፐር ደግሞ ከመመራት ተነስቶ ፉልሃም ላይ ድል አስመዝግቧል፡፡

የሀሪ ኬን እና ሰን ሁንግ ሚን ቦታን ይሸፍናል ተብሎ ተሰፋ የተጣለበት ፈርናንዶ ሎሬንቴ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሮ ፉልሃምን መሪ ቢያደርግም በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ደሊ አሊ እንዲሁም ሃሪ ዊንክስ ያስቆጠራት የተጨማሪ ደቂቃ ግብ 2 ለ 1 በመሸነፍ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አሳክቷል፡፡

ማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ቡድናቸው ድል አስመዝግቦ እፎይ ቢሉም አሊን በጉዳት ምክንያት ማጣታቸው ሌላ ተጨማሪ ጭንቀት ውስጥ ከትቷቸዋል፡፡

ሊጉን ሊቨርፑል በ60 ነጥብ ይመራል ፤ ማ.ሲቲ በ56 ሁለተኛ፤ ቶተንሀም በ51 ሶስተኛ፤ ቼልሲ በ47 ነጥብ አራተኛ እንዲሁም አርሰናል እና ማ.ዩናይትድ በ44 ነጥብ አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *